የእኛ ስራ

የሰራተኛ መብቶች ህብረት የአሰራር ዘዴ

ሰራተኞች ስለማንኛውም የስራ ቦታ መረጃ ተመራጭ ምንጭ ናቸው፣ ስለዚህም እነሱ የሰራተኛ መብቶች ህብረት የምርመራ ዘዴ ትኩረት ናቸው። በወሳኝነት፣ የሰራተኛ መብቶች ህብረት ሰራተኞች ከስራ ቦታቸው ውጪ፣ ያለ ፋብሪካው አስተዳደር እውቅና ወይም ጣልቃ ገብነት ለሰራተኞች ቃለ መጠይቅ ያደርጋል፣ ይህ ሰራተኞች በግልፅ እና ያለ በቀል ፍራቻ እንዲናገሩ ይረዳል። ብራንዶች የኮንትራት አቅራቢዎቻቸውን ሲመረምሩ ሠራተኞችን በፋብሪካው ውስጥ ያነጋግራሉ፣ ይህም ትንሽ ወይም ግልጽ ያልሆነ መረጃ እንደሚያገኙ ያረጋግጣለ። ይህ የሰራተኛ መብቶች ህብረት በብራንዶቹ እና በመርማሪዎች በመደበኛነት የሚታልፉ የሰራተኛ መብት ጥሰት እንዲያጋልጥ ያስችለዋል።

የሰራተኛ መብቶች ህብረት ከማህበራት፣ ከሰብአዊ መብት ቡድኖች፣ ከሴቶች ድርጅቶች እና በአለም ዙሪያ ካሉ ሌሎች የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች ጋር ሰፊ የግንኙነት መረብ የገነቡ አለምአቀፍ የመስክ መርማሪዎችን ይዟል። እንደ ሥራችን አካል፣ የሰራተኛ መብቶች ህብረት በምንመረምራቸው ፋብሪካዎች የተገኙ ውጤቶችን፣ የብራንዶችን፣ ቸርቻሪዎች እና የፋብሪካ ባለቤቶች ለእነዚያ ግኝቶች የሰጡትን ምላሽ ያካተተ ዝርዝር የህዝብ ሪፖርቶችን ያቀርባል። የሰራተኛ መብቶች ህብረት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ብራንዶችን እና አቅራቢዎቻቸውን ወሳኝ የሚባሉ መፍትሄዎችን ማለትም ለሠራተኞች ያልተከፈሉ ክፍያዎችን ማስከፈል፣ ያለአግባብ ከሥራ የተባረሩ ሠራተኞች ወደ ነበሩበት መመለስ እና  የደህንነት ማሻሻያዎች ስራዎች በአስገዳጅነት እንዲያከናውኑ አድርጓል፡፡

 

በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ የስርዓት ለውጥ

የሰራተኛ መብቶች ህብረት ጥረቶች በአለምአቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያለውን የሰራተኛ መብት ጥሰት ተፈጥሮን እና መንስኤዎችን በማሳየት፣ በኢንዱስትሪ የተደገፉ የክትትል መርሃ ግብሮች በቂ አለመሆንን በማጋለጥ እና ስለ እውነተኛ ማሻሻያ መንገድ የሚደረጉ ህዝባዊ ክርክሮችን ቅርጽ በማስያዝ ረድተዋል።

በአቅርቦት ሰንሰለቶች ውስጥ የተሻለ ሁኔታዎችን ለማስፈን የስርዓት ማሻሻያ ይጠይቃል ይህም የበጎ ፍቃደኛ የኢንዱስትሪ ቃል ኪዳኖች፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚ በሚሆኑ እና ብራንዶች በአቅራቢዎች ላይ የሚያደርሱትን የዋጋ ጫና እንዲያቆሙ በሚያስገድዱ ስምምነቶች መተካትን ያጠቃልላል፡፡ እኛ ይህንን ስትራቴጂ የሚያራምድ አጀንዳ እንመራለን።

በኡዩጉርን የግዳጅ ስራ ማስወገጃ ጥምረትን፣ በሌሴቶ የሚገኙ የኒየን ሂሲንግ የሰው ሃይልን በአጠቃላይ የሚሸፍን ጻታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት እና ትንኮሳ ስምምነትበባንግላዲሽ የእሳት እና የግንባታ ደህንነት ስምምነት፣ የአልታ ግራሲያ የኑሮ ምጣኔን መሰረት ያደረገ ደሞዝ ልብስ ፋብሪካ እና በሆንዱራስ ያሉትን የፍሩት ኦፍ ሉም የሰው ኃይልን የሚያጠቃልል እና የመደራጀት መብትን የሚያረጋግጥ የህብረት አስተዳደር ስምምነት ያካተቱ አዲስ እና ውጤታማ የሆኑ የሰራተኛ መብቶች ማሻሻያዎችን በማዘጋጀት እና በማስጀመር ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫውተናል።