ስለ

የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ራሱን የቻለ የሰራተኛ መብት ክትትል ድርጅት ነው። በዓለም ዙሪያ ባሉ ፋብሪካዎች ውስጥ የስራ ሁኔታዎችን እንመረምራለን። የእኛ ዓላማ የጉልበት ብዝበዛ ሁኔታዎችን ለመመዝገብ እና ለመዋጋት፤ የሰራተኛ መብት ጥሰትን የሚያራምዱ የአለም አቀፍ ብራንዶች እና ቸርቻሪዎችን አሰራር መለየት እና ማጋለጥ እና አልባሳት እና ሌሎች ምርቶችን የሚያመርቱ ሰራተኞችን መብቶች መጠበቅ ነው።

የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ገለልተኛ፣ ሰራተኛን ያማከለ ምርመራዎችን ያካሂዳል፤ ለዋና ዋና ብራንዶች በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ላይ ህዝባዊ ሪፖርቶችን ያወጣል ፤ እንዲሁም በእነዚህ ፋብሪካዎች ውስጥ ያሉ ጥሰቶችን ለማስቆም እና የስራ ቦታ መብታቸውን ለማስጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሰራተኞች እገዛ ያደርጋል። የሰራተኛ መብቶች ጥምረት በብዙ አገሮች ውስጥ መርማሪዎች ያሉት ሲሆን በደቡብ ምሥራቅ እስያ፣ ምስራቅ እስያ፣ ደቡብ እስያ፣ አሜሪካ እና አፍሪካ በመቶ ከሚቆጠሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ይሰራል።

ለአለም የማኑፋክቸሪንግ ሰራተኞች ጥሩ ሁኔታዎች እና ደሞዝ ለማመቻቸት በአለምአቀፍ የታዋቂ ብራንዶች የምርት ሰንሰለቶች ላይ ብራንዶች እና ቸርቻሪዎች በፈቃደኝነት ሊፈጽሙት ያልቻሉት የስርዓት ለውጥ ሊመጣ ያስፈልጋል። ለዚህ ዓላማ ከፋብሪካ-ተኮር ሥራችን በተጨማሪ፣  የሰራተኛ መብቶች ጥምረት በሠራተኛ ተወካዮች እና በአለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች መካከል አስገዳጅ ስምምነቶችን ለመፍጠር ይፈልጋል። ትርጉም ያለው ህዝባዊ የስራ ሁኔታ የምዘና መለኪያዎች የማስከበር ስራ አነስተኛ በሆነበት እና በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ "የድርጅት ማህበራዊ ሃላፊነት" መርሃ ግብሮች ሰራተኞችን ለመጠበቅ በተሳናቸው የአለም ኢኮኖሚ ውስጥ፣ ተፈጻሚ የሚሆኑ የግል ስምምነቶች - እንደ በባንግላዲሽ የእሳት አደጋ እና የግንባታ ደህንነት ስምምነት ያሉ ለሰራተኞች ተጨባጭ ጥቅሞችን ለመፍጠር የሚገኙ ምርጥ ዘዴዎች በመፍጠር እና በመተግበር የሰራተኛ መብቶች ጥምረት እገዛ አድርጓል።

እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም በአለም አቀፍ የሰራተኛ መብት ባለሙያዎች ፣ ተማሪዎች እና ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች የተመሰረተው የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ለዩንቨርስቲዎች፣ አልባሳትን እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲ አርማዎችን ያደረጉ እቃዎችን የሚያመርቱ ሰራተኞች መብትን ለመጠበቅ ያወጧቸው አስገዳጅ የስራ ሁኔታ ምዘና መለኪያዎችን ለማስከበር በሚያደርጉት ጥረት እገዛ ያደርጋል። የሰራተኛ መብቶች ጥምረት በዩናይትድ ስቴትስ እና በካናዳ ውስጥ በርካታ የዩኒቨርሲቲ እና የኮሌጅ ተባባሪዎች አሉት። የሰራተኛ መብቶች ጥምረት የሰብአዊ መብት መስፈርቶችን ለማስከበር የከተማ አስተዳደሮችን እና የጡረታ ፈንዶችን ጨምሮ ከመንግስት አካላት ጋር ይሰራል።