በባንግላዲሽ ውስጥ የግንባታ እና የእሳት ደህንነት ላይ የተደረገ ስምምነት

ባንግላዲሽ አልባሳትን ወደ አሜሪካ በመላክ አራተኛ ደረጃን ትይዛለች። የልብስ ዘርፍ ከአገሪቱ የወጪ ንግድ 80 በመቶውን የሚይዝ ሲሆን ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰራተኞች በስሩ አሉት። እነዚህ ሰራተኞች በኢንዱስትሪው ውስጥ የድህነት ደሞዝ፤ የቃላት እና የአካል ትንኮሳ፤ ለተሻለ ሁኔታ በመሟገት ብቀላ እና እጅግ በጣም አስተማማኝ ያልሆኑ የፋብሪካ ሕንፃዎችን ጨምሮ በጣም አስከፊ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል፡፡

ከ 2005 ዓ.ም ጀምሮ እነዚህ አደገኛ የእሳት እና የህንፃ ደህንነት ሁኔታዎች መከላከል ሲቻል ወደ 2,000 የሚጠጉ የባንግላዲሽ ሰራተኞችን በአሳዛኝ ሁኔታ ገድለዋል፡፡ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በሚያዝያ 2013 ዓ.ም የራና ፕላዛ ህንፃ ወድቆ 1,134 ሰራተኞች ሞተዋል፣ ይህም በኢንዱስትሪው ታሪክ ውስጥ ከታዩት የከፋ አደጋ ነው። በራና ፕላዛ ያሉ ፋብሪካዎች ጄሲፔኒ፣ ዘ ቺልድሬንስ ፕሌስን እና ዋልማርትን ጨምሮ ለብዙ ዋና ዋና ብራንዶች እና ቸርቻሪዎች የሚያመርቱ ነበር። አብዛኛዎቹ እነዚህ ኩባንያዎች ፋብሪካው ከመፍረሱ በፊት ባሉት ወራት ውስጥ ኦዲት ያደርጉ ነበር— ነገር ግን እነዚህ ኦዲቶች ለአደጋ የሚዳርጉትን የደህንነት ጥሰቶች መለየት ወይም ማስተካከል አልቻሉም።

 

አዲስ ሞዴል፡ ስምምነቱ

እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ 2013 ዓ.መ ራና ፕላዛ ሲፈርስ ፣ የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ቀድሞውኑ በባንግላዲሽ በሚገኙ አቅራቢ ፋብሪካዎች ላይ እውነተኛ የደህንነት ማሻሻያዎችን ለማምጣት የልብስ ብራንዶችን የእሳት እና የግንባታ ደህንነት አካሄዳቸውን በመሠረታዊነት ለመለወጥ በመጫን ለአመታት ሲሰራ ነበር። አደጋውን ተከትሎ የተፈጠረው አለማቀፋዊ ትኩረት ብራንዶችን ወደ ድርድር ጠረጴዛው እንዲመለሱ ያስገደዳቸው ሲሆን፤ የሰራተኛ መብቶች ጥምረት እና አጋሮቻችን ታሪካዊውን የባንግላዲሽ የግንባታ እና የእሳት ደህንነት ስምምነትን በተሳካ ሁኔታ እንዲፈርሙ ማሳመኛ ሆኗቸዋል። ስምምነቱ በሠራተኞች፣ በፋብሪካ አስተዳዳሪዎች እና በአልባሳት ኩባንያዎች መካከል የተደረገ የመጀመሪያው የዘመናችን አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት ሲሆን ብራንዶች እና ቸርቻሪዎችን የሚከተሉትን ዝርዝር ሁኔታዎች እንዲተገብሩ ይጠይቃል፡

  • የአቅራቢ ፋብሪካዎች በብቁ ባለሙያዎች እና መሐንዲሶች ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆኑ ፍተሻዎች እንዲደረግባቸው መፍቀድ፤
  • የእነዚህን ፍተሻ ውጤቶች በይፋ፣ ሊፈለግ በሚችል የውሂብ ጎታ - ሰርቸብል ዳታ ቤዝ ውስጥ እንዲካተት መፍቀድ፤
  • አስፈላጊ ለሆኑ የደህንነት እድሳት ክፍያ እገዛ ማድረግ፤
  • አስፈላጊውን የደህንነት ማሻሻያ ካላደረጉ ከማንኛውም ፋብሪካዎች ጋር የንግድ ሥራ መሥራት ማቆም፤

በተጨማሪም ስምምነቱ ሰራተኞች በፋብሪካቸው ውስጥ ሊደርሱ የሚችሉ ጥሰቶችን ለስምምነቱ ማንነታቸው ሳይገለጽ ሪፖርት ማድረግ የሚችሉበትን የቅሬታ ዘዴ ይዘረዝራል። ሕጋዊ ባልሆኑ ፈራሚዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድበት የማስፈጸሚያ ዘዴንም ያካትታል።

ስምምነቱ በልብስ ፋብሪካዎች ላይ የደህንነት ጥሰቶች አፈታት መሰረታዊ ለውጥን ያመላከተ ነው። ከዚህ ቀደም በድርጅት የሚመሩ ፕሮግራሞች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረቱ ሆነው የማስፈጸሚያ ዘዴዎች እና ግልጸኝነት የሚጎላቸው ነበሩ። በስምምነቱ መሰረት ብራንዶች እና ቸርቻሪዎች ልብሳቸውን የሚሰሩ ሰራተኞች በአስተማማኝ የስራ ሁኔታ ውስጥ የሚሰሩ መሆናቸውን የማረጋገጥ ህጋዊ ሃላፊነት አለባቸው።

 

ስምምነቱ ዛሬ ላይ

ዛሬ ወደ 200 የሚጠጉ ብራንዶች እና ቸርቻሪዎች የ2018ቱን ስምምነት የፈረሙ ሲሆን ይህም የመጀመሪያውን ዋና ስምምነት ለተጨማሪ ሶስት አመታት ያራዝመዋል። ከፈራሚ ብራንዶች ሦስቱ በዓለም ላይ ካሉት አራት ትልልቅ የፋሽን ቸርቻሪዎችን - ኤች ኤንድ ኤም፣ ኢንዲቴክስ እና ዩኒክሎ ያካትታሉ። እነዚህ ብራንዶች በአንድ ላይ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሠራተኞችን ቀጥረው ከሚያሰሩ 1,600 በላይ አቅራቢ ፋብሪካዎች ጋር ይሰራሉ።

በእነዚህ ፋብሪካዎች ላይ በተደረገው ፍተሻ ወደ 130,000 የሚጠጉ የደህንነት ጥሰቶች ታይቷል፡፡ ይህም ከመዋቅራዊ ጉዳት እስከ ደህንነቱ ያልተጠበቀ የእሳት ማምለጫ መንገዶች ናቸው፡፡ እስካሁን ባለው ጊዜ፣ አብዛኛዎቹ እነዚህ የደህንነት አደጋዎች ተወግደዋል።

ሰኞ ሰኔ 1 ቀን የባንግላዲሽ የስምምነቱ ጽህፈት ቤት ተግባራቶቹን በቅርቡ ወደ ተቋቋመው የሀገር ውስጥ ድርጅት የተዘጋጁ ልብሶች ዘላቂነት ካውንስል (አርኤስሲ) አሸጋግሯል።  አርኤስሲ በባንግላዴሽ ውስጥ ስምምነቱ ያካተታቸውን የደህንነት ፕሮግራሞች ፈጻሚ ወኪል ሆኖ ሲዋቀር ስምምነቱን እንዲተካ በማሰብ አደለም። በስምምነቱ ስር የተቀመጡ የብራንድ ኃላፊነቶች ስምምነቱ እስከ ሚያበቃበት ጊዜ ማለትም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ 2021 ዓ.ም በስራ ላይ የሚቆዩ እና የማይለወጡ ናቸው፡፡ በልብስ ብራንድ እና በማህበር ፈራሚዎች መካከል በስምምነቱ ዙሪያ ያለው ወቅታዊ ድርድር ግን የስምምነቱ ጊዜ እንደሚራዘም እና በደቡብ እስያ በሚገኙ ሌሎች አገሮች የፋብሪካ ደህንነት ፕሮግራሞችን አስፍቶ ለመሸፈን ያለሁኔታን የሚያመላክት ነው።

 

የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ሚና

ስምምነቱን በመተግበር እና በማስፈጸም ረገድ የሰራተኛ መብቶች ጥምረት ወሳኝ ሚና መጫወቱን ቀጥሏል። የስምምነት አስተባባሪ ኮሚቴ ምስክር ፈራሚ እንደመሆኑ፣ የሰራተኛ መብቶች ጥምረት የስምምነቱ መርሆች ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር የሚሰራ ሲሆን ቁጥጥር እና ጥገናም ጊዜውን በጠበቀ መልኩ እየተካሄደ ነው።