የፋብሪካ ዳታቤዝ

የሰራተኛ መብቶች ጥምረት በጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ውስጥ ግልፅነትን ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት አማካኝነት በድረገጻችን የኮሌጆችን እና የዩኒቨርሲቲዎችን ስም እና አርማ ያላቸውን እቃዎች የሚያመርቱ በአለም ዙሪያ የሚገኙ የልብስ ፋብሪካዎች ዳታቤዝ አዘጋጅቶ ይዟል። የመረጃ ቋቱ የፋብሪካዎች ስም እና ቦታ፣ የሚያመርቷቸው ምርቶች እና ሌሎች መረጃዎችን ያካትታል። እዚህ በመጫን የመረጃ ቋቱን ማግኘት ይችላሉ።

ይህን ዳታቤዝ ለመጠቀም በእንግሊዝኛ የአንዳንድ መሰረታዊ ቃላት እውቀት ሊኖርዎ ይገባል፡-

  • ለአንድ የተወሰነ ዩኒቨርሲቲ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ለመፈለግ የዚህን ዩኒቨርሲቲ ስም SCHOOL ማውጫ ከሚለው ስር ይምረጡ
  • ለአንድ የተወሰነ የምርት ስም የሚያመርቱትን ፋብሪካዎች ለማግኘት LICENSEE ከሚለው ማውጫ ውስጥ የዚህን የምርት ስም ይምረጡ፤
  • በአንድ ሀገር ውስጥ የሚያመርቱትን ፋብሪካዎች ለማግኘት COUNTRY ከሚለው ማውጫ ውስጥ የዚህን ሀገር ስም ይምረጡ።
  • የተለየ ፋብሪካ ለመፈለግ የዚህን ፋብሪካ ስም FACTORY በሚለው ሳጥን ውስጥ ይተይቡ።
  • እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን ምርጫዎች በማጣመር ፍለጋ ማድረግ ይችላሉ።

መረጃውን በሚያስገቡበት ጊዜ ውጤቱን በሚከተሉት መንገዶች ማየት ይችላሉ:-

  • ለአንድ የተወሰነ ትምህርት ቤት የሚያመርቱትን የፋብሪካዎች ዝርዝር ብቻ ለማየት፣ GROUP BY ማውጫ ይጫኑ እና SCHOOL ይምረጡ።
  • ለአንድ ሀገር የሚያመርቱትን ፋብሪካዎች ዝርዝር ብቻ ለማየት፣ GROUP BY ማውጫ ላይ ይጫኑ እና COUNTRY የሚለውን ይምረጡ።
  • ለአንድ የተወሰነ የምርት ስም የሚያመርቱትን የፋብሪካዎች ዝርዝር ብቻ ለማየት፣ GROUP BY ማውጫ ላይ ይጫኑ እና LICENSEE ይምረጡ።

የፋብሪካዎችን ዝርዝር ለማየት GROUP BY ማውጫ ላይ ይጫኑ እና FACTORY ይምረጡ። ይህ በነባሪነት ይመረጣል::